አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አገራቸው ተመለሱ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በኢትዮጵያ የቆዩትን ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ዛሬ ሽኝት አድርገውላቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷”ውዱ ወንድሜ ሼክ ሙሀመድ ቢን ዛይድ በኢትዮጵያን በነበራቸው ቆይታ በጣም ደስ ብሎኛል” ብለዋል።
“የጋራ የትብብር አድማሳችንን ማስፋት እንቀጥላለን” ሲሉም ገልጸዋል፡፡