የሀገር ውስጥ ዜና

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ስፔናዊው አትሌት የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ አገኘ

By Shambel Mihret

August 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ በሚገኘው በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ስፔናዊው አትሌት አልቫሮ ማርቲን የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ አገኘ።

አትሌቱ በ20 ኪሎ ሜትር የርምጃ ውድድር አሸናፊ በመሆን ነው የሻምፒዮናውን የመጀመሪያ ወርቅ ለማንሳት የቻለው።

ውድድሩን 1:17:32 በሆነ ሰዓት ሲያጠናቅቅ አትሌት አልቫሮ ማርቲንን በመከተል ስዊድናዊው አትሌት ፐርሴውስ ካርልስትሮም 1:17:39 በሆነ ሰዓት በመግባት የብር ሜዳሊያ አግኝቷል።

ብራዚላዌው አትሌት ካዮ ቦንፊም 1:17:47 በሆነ ሰዓት በመግባት የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቱን የዓለም አትሌቲክስ ያወጣው መረጃ አመልክቷል።