የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አመራሮች ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

May 08, 2020

አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የበላይ ጠባቂ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የኮቪድ19 ወረርሽኝን በተመለከተ ከማህበሩ አመራሮች ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ማህበሩ ወረርሽኙን በመከላከል ሂደት ውስጥ ያለውን ቁልፍ ሚና የበለጠ እንዲያጠናክር መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።