የሀገር ውስጥ ዜና

በነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር ) የተመራ ልዑክ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኘ

By Meseret Awoke

August 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) የተመራ የክልሉ ልዑክ በግንባታ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱም ÷ የዋቻ ከተማ ንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ እና የቦባ ቆቻ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን ተመልክቷል፡፡

እንዲሁም የዋቻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሥራ እንቅስቃሴን መጎብኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ጥር 2014 የተጀመረው የዋቻ ከተማ ንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ 85 በመቶ መድረሱ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ግንባታውን በመስከረም 2016 ለማጠናቀቅ እየተሰራ ስለመሆኑም የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ በየነ በላቸው (ኢ/ር) ተናግረዋል ።

ግንባታው ሲጠናቀቅም÷ ከ49 ሺህ 835 በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ለከተማው ንጹህ መጠጥ ውሃ ከ228 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መመደቡንም አመላክተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!