አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ጎሮ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ::
አደጋው ከወልቂጤ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ከአነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የደረሰ ነው፡፡
በዚህም የ3 ሰዎች ህይወት ሲልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
በአደጋው 2 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረትም መወድሙ የተገለፀ ሲሆን ÷ የአደጋው መንስኤ ከተፈቀደ የፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ነው ተብሏል።