የሀገር ውስጥ ዜና

ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞች መኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

By Mikias Ayele

August 22, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የየኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞች መኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ኮሚሽኑ አንቴክስ ከተባለው ቴክስታይል አምራች ኩባንያ ጋር ነው ስምምነቱን የተፈራረመው፡፡

አምራች ኩባንያው አቅምን ባገናዘበ ወጪ ለሰራተኞች በ4 ሄክታር መሬት ላይ የመኖሪያ ህንፃዎችን የሚገነባ ሲሆን 5 ሺህ የሚሆኑ ሰራተኞችን የቤት ባለቤት እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ የሰራተኞችን የቤት ችግር በመቅረፍ በስራ ላይ ያላቸውን ትኩረት እና ምርታማነት በመጨመር ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል መባሉን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡