የሀገር ውስጥ ዜና

የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ውይይት እያካሄደ ነው

By Shambel Mihret

August 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ ሀገር አቀፍ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ÷ በሀገሪቱ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ሚኒስቴሮች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡

ዘርፉን የተመለከቱ ጥናቶች በውይይቱ ቀርበው ምክክር ይደረጋል መባሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎትን በማስተዋወቅ በኩል የዛሬው ውይይት ትልቅ ሚና እንዳለው ተመላክቷል፡፡