አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም÷ በገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት፣ በምግብ ዋስትና፣ በአፈር አሲዳማነት እና አፈር ጤንነት ላይ መምከራቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም÷ በሰፋፊ የግብርና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተገልጿል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!