የሀገር ውስጥ ዜና

በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ምርቶች ከመደበኛው ገበያ ባነሰ ዋጋ ለሕብረተሰቡ እየቀረቡ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

August 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በ172 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ምርቶች ከመደበኛው ገበያ ባነሰ እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ለሕብረተሰቡ እየቀረቡ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች የነዋሪውን የኑሮ ጫና በማቃለል እና የምርቶችን ዋጋ በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው መባሉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ገበያዎቹ ለማሕበረሰቡ አማራጭ የመገበያያ ስፍራ ከመሆን ባሻገር÷ የግብርና፣ የኢንዱስትሪና የፋብሪካ ምርቶችን በቀጥታ ለሸማቹ በማቅረብ ለምርቶች ዋጋ መረጋጋት አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ተብሏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!