አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን በኦሊምፒክ መድረክ በመወከል ቀዳሚ ከሆኑት መከካል አንዱ የሆነው ቦክሰኛ በቀለ አለሙ (ጋንች) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ኢትዮጵያን ሶስት ጊዜ በኦሊምፒክ የወከለው በቀለ ዓለሙ በ82 ዓመቱ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።
ቦክሰኛ በቀለ በሮም፣ በቶክዮ እና በሜክሲኮ ኦሊምፒክ በቦክስ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክሎ ተሳትፏል።
በሜሲኮው ኦሊምፒክ ተሳትፎ ሜዳሊያ ያገኘ ሲሆን በሌጎስ የአፍሪካ ሻምፒዮን መሆኑም የህይወት ታሪኩ ያስረዳል።
ቦክሰኛ በቀለ አለሙ የህይወት ታሪኩን የሚዳስስ “ያልተነገረለት የአገር ባለውለታ “በሚል ርዕስ በ2004 ዓ.ም መጽሐፍ ታትሞለታል።
በ1933 ዓ.ም ታህሳስ 29 ቀን የተወለደው ቦክሰኛ በቀለ አለሙ የ11 ልጆች አባት ነበር።
የቦክሰኛ በቀለ ዓለሙ የቀብር ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት 6 ሰዓት ላይ በሸጎሌ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።