የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ተገለጸ

By Alemayehu Geremew

August 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ተገለጸ፡፡

በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ቻም ኡጋላ ከሀገሪቷ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ማርቼንኮ ኢቭጄኒ ኢቭጄኒቪች ጋር በጉዳዩ ላይ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም ስለሁለቱ ሀገራት ዘመን ተሻጋሪ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማውሳታቸው እና ይኅን ታሪክ በምጣኔ ሐብታዊ ግንኙነትም መድገም እንደሚገባ መናገራቸውን በሩሲያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡