አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በ73ኛው የአፍሪካ አህጉር የዓለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ እየተሳተፈ ነው።
በመድረኩ ከ20 በላይ በሚሆኑ የተለያዩ የጤና አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የአፍሪካ ማህበረሰብ ጤና አሁናዊና ቀጣይ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ከዓለም ማህበረሰብ ጤና ጋር ያላቸው አጠቃላይ ሁኔታም በመድረኩ ይዳሰሳል ተብሏል፡፡
ከዚህ ባለፈም አራት የመፍትሄ ሃሳቦችን የያዙ ሰነዶች ቀርበው በአባል ሀገራቱ እንደሚጸድቁ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ የተለያዩ መግለጫዎችን በመድረኩ የምታቀርብ ሲሆን÷ በጎንዮሽ መድረክም ልዑካኑ እንደሚሳተፉ ተጠቁሟል፡፡
73 ኛው የአፍርካ አህጉር የዓለም ጤና ድርጅት መድረክ በቦትሰዋና ጋባሮኒ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡