የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አወል አርባ ከተመድ የኢትዮጵያ ተጠሪ ጋር ተወያዩ

By Alemayehu Geremew

August 28, 2023

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ ከተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ተጠሪ ራሚዝ አላክባሪቭ እና ልዑካቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በክልሉ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ሊደረጉላቸው ስለሚገቡ አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፎች አቶ አወል ገለፃ አድርገዋል፡፡

የክልሉን ሕዝብ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የክልሉ መንግስት በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑም ተብራርቷል፡፡

ራሚዝ አላክባሪቭ በበኩላቸው÷ የክልሉ ሕዝብ ያሉበትን ችግሮች ለመፍታት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከክልሉ መንግስትና ሕዝብ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡