የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮ- አውሮፓ ህብረት ግንኙነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

By Shambel Mihret

August 29, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአውሮፓ ሕብረት የወዳጅነት ቡድን ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያለውን የቆየ መልካም ግንኙነት የበለጠ በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡

የወዳጅነት ቡድኑ አባላት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት ተወካይ አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ ጋር በተወያዩበት ወቅት የመልካም አስተዳደር፣ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ የፓርላማ ዲፕሎማሲ አተገባበርና የምክር ቤት ስራዎችን የሚያሻሽሉ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡

ውይይቱ ፥ የኢትዮ-አውሮፓ ህብረት ግንኙነትን የበለጠ የሚያጠናክርና ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚያግዝ እንደሆነ መገለጹን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላከልታል፡፡