የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ጌታቸው ረዳ ከራሚዝ አልክባሮቭ (ዶ/ር) ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

August 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር ጌታቸው ረዳ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ራሚዝ አልክባሮቭ (ዶ/ር) ከተመራ ልዑክ ጋር በመቀሌ ተወያዩ።

በውይይታቸውም÷ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ፣ ሰብዓዊ ድጋፍ በተመለከተ፣ የአንበጣ መንጋን መከላከል በሚቻልበት አግባብ እና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አተገባበር እና በክልሉ ያለውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር በተመለከተ አቶ ጌታቸው አብራርተዋል፡፡

ራሚዝ ኣልክባሮቭ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በክልሉ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ እንሠራለን ማለታቸውን የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የልኡካን ቡድ አባላት ተፈናቃዮች በሚገኙበት ቦታ ተገኝቶ ምልከታ እንደሚያደርግም ተጠቁሟል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!