የሀገር ውስጥ ዜና

ሜታ ኩባንያ ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮች ስልጠና ሰጠ

By Shambel Mihret

August 30, 2023

ሜታ ኩባንያ ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮች ስልጠና ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሜታ ኩባንያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናው ኩባንያው በፌስቡክ፣ በዋትስ አፕና በኢንስታግራም የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ያካበተውን ተሞክሮ ለኢንስቲትዩቱ ለማጋራት እና አብሮ ለመስራት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ስልጠናው በዘርፉ የላቀ እውቀት እና ክህሎት ያላቸውን የመስኩ ምሁራን በመላክ የተሰጠ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመላታክል፡፡