ስፓርት

ንግድ ባንክ በምስራቅ አፍሪካ የቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ

By Mikias Ayele

August 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በምስራቅ አፍሪካ የቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡

በውድድሩ ፍፃሜ የታንዛኒያውን ጀኬቲ ኩዊንስ የገጠመው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ÷ መደበኛ ጨዋታውን በአቻ ውጤት ማጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት አምርተዋል፡፡

በዚህም 5 ለ 4 ተሸንፎ ዋንጫውን አጥቷል፡፡

ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያን የወከለው ንግድ ባንክ ውድድሩን በሁለተኛነት ለማጠናቀቅ ተገዷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም የምስራቅ አፍሪካ ሻምፒዮን የሆነው ጄቲኬ ኩዊንስ በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት በሚከናወነው ዋናው የቻምፒየንስ ሊግ ውድድር መሳተፉን አረጋግጧል።