አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዶራሌ ሁለገብ ወደብ እና የጅቡቲ ካርጎ ተርሚናል አስተዳደራዊ የአሠራር ክፍተቶችን በመቅረፍ የዝውውር ፍሰትን ማቀላጠፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከስምምነት ተደርሷል።
በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ ወደቦች ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ሊቀመንበር አቡባከር ኦመር ሀዲ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ የኢትዮ-ጂቡቲ ኮሪደር እንቅስቃሴ እና የወደብ ሥራ አገልግሎት አቅም ማሻሻል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከራቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም ለሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክተው የዶራሌ ሁለገብ ወደብ እና የጅቡቲ ካርጎ ተርሚናል አስተዳደራዊ የአሠራር ክፍተቶችን በመቅረፍ የዝውውር ፍሰትን ማቀላጠፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ከስምምነት ተደርሷል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!