የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

August 31, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ከተለያዩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ ላይ÷ በክልሉና በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ፣ የፖለቲካ እና የጸጥታ ጉዳዮችና ቀጣይ እቅዶች እንዲሁም አመራሮቹ በቀጣይ ትኩረት ሰጥተው ሊያከናውኗቸው በሚገቡ ስራዎች ዙሪያ ማብራሪያና የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኢብራሂም ኡስማን፣ በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢ/ር መሐመድ ሻሌና ሌሎች አመራሮች መሳተፋቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡