ዓለምአቀፋዊ ዜና

የአፍሪካ ህብረት ጋቦንን ከአባልነት ተሳትፎ አገደ

By Melaku Gedif

September 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት በጋቦን የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ሀገሪቷን ከአባልነት ተሳትፎ ማገዱን አስታወቀ፡፡

የጋቦን ወታደራዊ አመራሮች በተያዘው ሳምንት የመንግስትን ስልጣን መቆጣጠራቸውን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ም/ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷የጋቦን ጦር በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ ላይ ያደረገውን መፈንቅለ መንግስት አውግዟል፡፡

ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ በ ሀገሪቱ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 64 ነጥብ 27 በመቶ ድምጽ በማግኘት ለ3ኛ የስልጣን ዘመን መመረጣቸው ይፋ ተደርጎ ነበር፡፡

ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎም የአፍሪካ ህብረት ጋቦንን ከየትኛውም የአባልነት ተሳትፎ ማገዱን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡