የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል እየለማ ያለ የበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜትን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

September 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሰሜን ሲዳማ ዞን ሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሳማ ኤጄርሳ ቀበሌ በ100 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ ያለ የበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜትን ጎብኝተዋል።

የበቆሎ ዘር ብዜቱ በዘር አቅርቦት ፍላጎት ላይ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል እንደሚሆን በጉብኝቱ ወቅት መገለጹን የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በ100 ሄክታር መሬት ላይ ‘BH 546’ እና ‘BH140’ የተሻሻሉ የበቆሎ ዘሮች ብዜት መከናወኑ ተገልጿል፡፡

እስከ 2 ሺህ 500 ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!