የሀገር ውስጥ ዜና

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሐረሪ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ አከናወነ

By Alemayehu Geremew

September 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሐረሪ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ አከናወነ፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ ÷ በጎ ሥራ ለትውልድ ስንቅ ማስቀመጥ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብሩቱካን አያኖ ተናግረዋል።

ሚኒስቴሩ ÷ ለትምህርት ቤቶች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎችም የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተደድር ኦርዲን በድሪ በበኩላቸው ÷ በጎ ፈቃድ ለሰው ልጆች የተሰጠ የመልካምነት ማሳያ በመሆኑ ሁሉም በሚችለው አቅም በበጎ ፈቃድ ተግባራት ሊሳተፍ ይገባል ብለዋል።

የትምህርት ቁሳቁስ የተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች እና ተማሪዎችም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን አመሥግነዋል።

በምንያህል መለሰ