MOSCOW, RUSSIA - APRIL 6, 2020: Medical workers in protective suits handle equipment in a building repurposed by Sechenov First Moscow State Medical University as a hospital with a bed capacity of 210, to admit patients suspected of, or diagnosed with, the COVID-19 infection. Vladimir Gerdo/TASS Ðîññèÿ. Ìîñêâà. Ìåäèöèíñêèå ñîòðóäíèêè â ïîìåùåíèè ïåðåïðîôèëèðîâàííîãî ïîä ëå÷åíèå áîëüíûõ ñ èíôåêöèåé COVID-19 êîðïóñà Ïåðâîãî ìîñêîâñêîãî ãîñóäàðñòâåííîãî ìåäèöèíñêîãî óíèâåðñèòåòà èìåíè È.Ì.Ñå÷åíîâà.  óíèâåðñèòåòå îòêðûëñÿ öåíòð ïî îêàçàíèþ ìåäèöèíñêîé ïîìîùè ïàöèåíòàì ñ èíôåêöèåé COVID-19 íà 210 êîåê. Âëàäèìèð Ãåðäî/ÒÀÑÑ

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በሩስያ የመተንፈሻ መሳሪያ ከመጠን በላይ በመሞላቱ በደረሰ ቃጠሎ አምስት የኮሮናቫይረስ ህመምተኞች ህይወታቸው አለፈ

By Meseret Demissu

May 12, 2020

አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በሩስያ ከመጠን በላይ በተሞላ የመተንፈሻ መሳሪያ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አምስት በጽኑ ህሙማን ክፍል ሲታከሙ የነበሩ የኮሮና ቫይረስ ህመምተኞች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

የመተንፈሻ መሳሪያዎች አቅማቸው ውስን በመሆኑና ከመጠን በላይ በመሞላታቸው ለእሳቱ መከሰት ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው።

የሩሲያ የአደጋ ጊዜ ጉዳይ ሚኒስቴር÷ በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ በአደጋው በጽኑ የህሙማን ክፍል ውስጥ የነበሩ ህመምተኞች መሞታቸውን አረጋግጧል።

ከዚያም ባለፈ 150 ሰዎች ከሆስፒታሉ እንዲወጡ ተደርገዋልም ነው ያሉት።

በተመሳሳይ ባለፈው ቅዳሜ በመተንፈሻ መሳሪያ ላይ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በኮሮናቫይረስ በሽታ የተያዙ ህመምተኞችን ሲያክም የነበረ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉም ነው የተነገረው።

በሩሲያ አዳዲስ በኮሮናቫይረስ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በ11 ሺህ 656 ያደገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በሀገሪቱ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 221 ሺህ 344 ደርሷል።

ምንጭ፦ ሮይተርስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision