የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገር ከማገልገል በላይ ጀግንነት የለም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

By Shambel Mihret

September 06, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር ከማገልገል በላይ ጀግንነት የለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ዛሬ በፌዴራል የመንግሥት ተቋማት ከ38 ዓመታት በላይ ካገለገሉ ጀግኖች ጋር የአገልጋይነት ቀንን አብረን አክብረናል ሲሉ ገልጸዋል።

በመልዕክታቸውም ሀገር ከማገልገል በላይ ጀግንነት የለም ብለዋል።

እነዚህ አንጋፋዎች ለተተኪው ትውልድም አርዓያዎች ናቸውም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።