የሀገር ውስጥ ዜና

ጳጉሜን 2 የመስዋዕትነት ቀን በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው

By Melaku Gedif

September 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜን 2 የመስዋዕትነት ቀን በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው፡፡

ቀኑ “በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

ጠዋት 5 ሰዓት ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባለበት ቆሞ ቀኝ እጅን ወደ ላይ በማንሳት”እኔ የኢትዮጵያ የፀጥታ፣ የመረጃ እና የደኅንነት ተቋማት ለከፈሉት እና እየከፈሉት ላለው መስዋዕትነት ክብር እሰጣለሁ!” የሚል መልዕክት እንደሚያስተላልፍ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት ዘርፍ ለሀገሩ የሚጠበቅበትን መስዋዕትነት ለመክፈል በብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃል እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡