አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜን 2 የመስዋዕትነት ቀን በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ተከበረ፡፡
ቀኑ “በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ ተከበረ፡፡
ጠዋት 5 ሰዓት ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባለበት ቆሞ ቀኝ እጅን ወደ ላይ በማንሳት”እኔ የኢትዮጵያ የፀጥታ፣ የመረጃ እና የደኅንነት ተቋማት ለከፈሉት እና እየከፈሉት ላለው መስዋዕትነት ክብር እሰጣለሁ!” የሚል መልዕክት እንደሚያስተላልፍ ተገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈም ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት ዘርፍ ለሀገሩ የሚጠበቅበትን መስዋዕትነት ለመክፈል በብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃል እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!