አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የፀጥታ ተቋማት ውስጥ አባል ሆነው ሀገራቸውን እያገለገሉና መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ አካላት የኢትዮጵያ ጀግኖች ናቸው ሲሉ የጋምበሌላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ተናገሩ፡፡
“በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ የመስዋዕትነት ቀን ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ኢትዮጵያን በመስዋዕትነታቸው ያጸኑ ጀግኖችን በመዘከርና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በአከባበሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ ጠንካራና ሉዓላዊነቷ የተከበረች ሀገር ሆና እንድትቀጥል ሕዝቡ ሰላሟንና አንድነቷን ማስቀጠል ይጠበቅበታል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ቾል ኩን በበኩላቸው÷ በሀገሪቷ የተከሰቱ የጸጥታ ችግሮችን ለማስቆም መስዕዋትነት የከፈላችሁና እየከፈላችሁ የምትገኙ የፀጥታ አካላት ውለታችሁ አይዘነጋም ብለዋል ።
በጋምቤላ ክልል በገጠሙ ችግሮች የክልሉን ሰላም ለማስቀጠል መስዋዕትነት ለከፈሉ የፖሊስ አባላት ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!