አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ታላቅ ተጋድሎ የቆመችን ሀገር ለማስቀጠል ሁሉም በተሰማራበት መስክ መስዋዕትነት መክፈል ይገባዋል ሲሉ ጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባላት ገለጹ።
ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የመስዋዕትነት ቀን “በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር!” በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ ነው፡፡
የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባላት እየተከበረ ያለውን ቀን አስመልክቶ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ “አባቶቻችን የሀገርን ዳርድንበር ለማስከበር በዱር በገደሉ በከፈሉት የሕይወት መስዋዕትነት ሀገር በነፃነት እንድትቆይ አድርገዋል” ብለዋል፡፡
የጥንቱ የአርበኝነት ተጋድሎ ለነጻነት በሚከፈል የሕይወት መስዋዕትነት የሚገኝ መሆኑን ገልጸው÷ የአሁኑ ትውልድ ደግሞ በየመስኩ የተሰጠውን ኃላፊነት በተገቢው መንገድ በመወጣት አገርን የማፅናት መስዋዕትነት ሊከፍል ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
የአሁኑ ትውልድ ሀገሩ በምትፈልገው መስክ በተገቢው መንገድ በመሰማራት ኢትዮጵያን የማስቀጠል ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበትም ነው ያስገነዘቡት፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!