የሀገር ውስጥ ዜና

የመስዋዕትነት ቀን በአፋር ክልል እየተከበረ ነው

By Melaku Gedif

September 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜን 2 የመስዋዕትነት ቀን በአፋር ክልል በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው፡፡

ቀኑ “በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በተለያዩ ዝግጅቶች በሰመራ ከተማ እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በመርሐ ግብሩ የሕይወት መስዕትነት ለከፈሉ የሀገር መከላከያ የሰራዊት አባላት፣ ለአፋር ክልል ፖሊስ እና ለሌሎች ጸጥታ አካላት እውቅና ተሰጥቷል፡፡