አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጳጉሜ 2 የመስዋዕትነት ቀን “በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነዉ ፡፡
ቀኑን በማስመልከት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ባለው መድረክ በኢትዮጵያ በተከሰቱ የፀጥታ መደፍረስ ችግሮች ሀገርን ህልውና ለማስቀጠል መስዋዕትነት የከፈሉ የተለያዩ የፀጥታ ሃይሎችን የመዘከርና እውቅና መርሃ ግብር እንደሚከናዋን ይጠበቃል፡፡
በየደረጃው ያሉ የፀጥታ ሃይሎች ዜጎች በሠላም ወጥተው በሠላም እንዲገቡ ብዙ መስዋትነት መክፈሉን በመድረኩ መገለፁን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በአሁኑ ሰዓትም በመድረኩ መስዋዕትነት የፀናች ሀገር በሚል ለቀኑ የተዘጋጀ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል፡፡