የሀገር ውስጥ ዜና

601 የጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸው ተመላከተ

By ዮሐንስ ደርበው

September 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 የበጀት ዓመት በፌደራልና ክልሎች 301 ሺህ 664 ሄክታር ማልማት የሚችሉ 601 የጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ8 ክልሎች 230 ሺህ 964 ሄክታር የሚያለሙ 594 ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን መጠናቀቁን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

እንዲሁም በፌዴራል መንግስት ከሚተገበሩ 29 ፕሮጀክቶች መካከል 70 ሺህ 700 ሄክታር የሚያለሙ የሰባት ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን ተጠናቅቆ ለግንባታ ዝግጁ ሆኗል ብሏል፡፡

የጥናትና ዲዛይን ሥራው በሁለት ደረጃ ተከፍሎ የቅደመ አዋጭነት ስራውን በማስቀደም አዋጭነታቸው የተረጋገጠላቸው ፕሮጀክቶች ብቻ ወደ ዲዛይን ደረጃ እንዲያልፉ በማድረግ ጥራቱን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

በፕሮጀክት ግምገማውም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ የክልል ባለሙያዎች፣ ተጠቃሚው ማህበረሰብ እና ዘርፉን በዕውቀት ሊደግፉ የሚችሉ አማካሪዎችን በማሳተፍ ስኬታማ ሥራ ተከናውኗል መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም በፌደራል መንግስት በጀት ተመድቦላቸው 316 ሺህ 928 ሄክታር ማልማት የሚችሉ 16 የጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክቶች በጥናትና ዲዛይን ሂደት ላይ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

እንዲሁም ሌሎች ስድስት ፕሮጀክቶች የግዥ ሂደታቸው ተጠናቅቆና የመስክ ልየታ ተደርጎ የአዋጭነት ጥናት እየተሰራላቸው ይገኛል ነው የተባለው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!