የሀገር ውስጥ ዜና

የበጎነት ቀን በጋምቤላ እየተከበረ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

September 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የበጎነት ቀን በጋምቤላ ክልል “በጎነት ለሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡

ቀኑ በጎ ተግባራትን በማከናወን፣ ለሀገርና ለወገን የሚበጀውን በማድረግ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

ያለው ለሌለው በማካፈልና የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብ እየተከበረ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡