አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የበዓል ስጦታና ማዕድ ማጋራቱን አስታወቀ፡፡
ዛሬ “በጎነት ለሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ የበጎነት ቀን መልካም ተግባራትን በማድረግ እየተከበረ ነው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ÷ የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ለሕጻናትና በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች ስጦታና የማዕድ ማጋራት መከናወኑን ገልጸዋል።
ለበጎ ተግባሩ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ባዋጡት ገንዘብ ድጋፉ መደረጉን እና ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባለሀብቶችን በማስተባበር በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ከ15 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ ያስገነባቸውን 10 የአቅመ ደካማ ቤቶች አስተላልፏል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!