አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከቻይና ምክትል አምሳደር ሽን ከንሚን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ÷ ኢትዮጵያና ቻይና በጸረ-ሙስና ትግል በትብብር መስራት በሚችሉበት አግባብ ላይ መክረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ መጠነ ሰፊ ተሳትፎ የሚያደርጉ የቻይና ባለሃብቶች ከሙስና የፀዳ የስራ ምህዳር እንዲኖራቸው አስቻይ ሁኔታ መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል፡፡
በቻይና በሚደረገው የ “ክሊን ሲልክ ኤንድ ሮድ ፎረም” ወቅት በትብብር መሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡