የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ

By Feven Bishaw

September 08, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ፡፡

የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ጽህፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ህጻናት እና 250 አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ሰራተኞች የአዲስ ዓመት መዋያ ማእድ ማጋራት ተካሂዷል።

ዛሬ በመላ ሀገሪቱ “በጎነት ለሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ የበጎነት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡