ዓለምአቀፋዊ ዜና

በሞሮኮ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 300 የሚጠጉ ሰዎች ሕይዎት አለፈ

By Meseret Awoke

September 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ296 ሰዎች በላይ ሕይዎት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

6 ነጥብ 8 የሚለካው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ካደረሰው የሰው ሕይዎት መጥፋት ባሻገር እስካሁን 153 ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰም ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም ሕንፃዎች ፈርሰዋል፣ የኤሌክትሪክ ኃይል እና የቴሌፎን ኔትዎርክ ለ10 ደቂቃዎች መጥፋቱን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳሉት፥ ታዋቁ የቱሪስት መዳረሻ የሆነችውና በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበችው ማራካሽ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶባታል፡፡

ከማራካሽ ከተማ በስተደቡብ የሚገኙ አካባቢዎችም የጉዳቱ ሰለባ እንደሆኑም ተገልጿል።

በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊያይል እንደሚችልም ነው የተነገረው፡፡

#Morocco #earthquake

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!