የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በዚህ የሐዘን ወቅት ከሞሮኮ ጎን መቆሟን አስታወቀች

By Alemayehu Geremew

September 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በሞሮኮ በደረሰው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል።

አደጋውን ተከትሎም የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው÷ ኢትዮጵያ በዚህ አስቸጋሪ የሐዘን ወቅት ከሟች ቤተሰቦች እና ከሞሮኮ ሕዝብ ጋር እንደምትቆም ገልጿል፡፡

በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 8 የሚለካው በማዕከላዊ ሞሮኮ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስካሁን ከ820 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡