አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላማችንና አንድነታችንን በማጠናከር የክልላችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እንሰራለን ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ።
መስራች ጉባኤውን ዛሬ በካራት ከተማ ያካሄደው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት አቶ አዳማ ትንጳዬን አፈ-ጉባኤ እንዲሁም አቶ ዳርጌ ዳሼን ምክትል አፈ-ጉባኤ አድርጎ መሰየሙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አቶ ጥላሁን ከበደ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት በህገ-መንግስቱ መሠረት የዜጎችን መብት የማስከበር፣ በብሔረሰቦች መካከል የሚነሱ የማንነትና የወሰን ጥያቄዎች በአግባቡ እንዲፈቱ በማድረግ ትልቅ ኃላፊነት የተሰጠው መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የብሔረሰቦች ምክር ቤት አባላት የብሔረሰቦች ብቻ ሳይሆኑ መላውን ህዝብ ወክለው ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ማገልገል እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!