አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የአብሮነት እሴት እንዲጎለብት ሚናቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ።
ዛሬ በመላ ሀገሪቱ “በህብር የተሠራች ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ የሚገኘውን የአብሮነት ቀን ምክንያት በማድረግ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች እንዳሉት÷ የሕዝቦች አብሮነትና ትብብር ኢትዮጵያን በጋራ ያቆመ ምሰሶ ነው፡፡
የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሐሳብ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ችግሮችን በሰከነ መንፈስ ማለፍ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
ከሚያለያዩ ሐሳቦች ይልቅ የሚያቀራርቡት ላይ ትኩረት በማድረግ ለሀገር ግንባታ በጋራ መትጋት ይገባል ብለዋል፡፡
ወጣቶች የወደፊቷን ኢትዮጵያ በእኩልነት እና በመከባበር ላይ ለመገንባት የሚደረገውን ርብርብ በቅንነት ማገዝ እንዳለባቸውም ነው የመከሩት፡፡
የሃይማኖት ተቋማትና የሃይማኖት አባቶች በትውልዱ ላይ መስራት እንዳለባቸውም አመላክተዋል፡፡
ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ተተኪው ትውልድ ከሁሉ በላይ ችግሮችን በመነጋገር፣ በመመካከርና በሐሳብ የበላይነት የማመን ልምድን ሊያዳብር እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!