የሀገር ውስጥ ዜና

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ካቢኔ የመጀመሪያ ስብሰባውን አካሄደ

By Shambel Mihret

September 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ካቢኔ የመጀመሪያ ስብሰባውን በሆሳዕና ከተማ አካሂዷል።

ካቢኔው በስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ መመስረቱ ይታወሳል።