አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ለ1 ሺህ 205 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ሃላፊ አቶ ማቶ ማሩ እንደገለፁት÷ የክልሉ ርዕሰ መስተደድር የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለታራሚዎቹ ይቅርታ አድርገዋል።
ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል 12ቱ ሴቶች መሆናቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡
ታራሚዎቹ የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ወደ ማረሚያ ተቋማት ገብተው እንደነበር ጠቅሰው÷ በቆይታቸውም መልካም ስነ ምግባር ያሳዩ እንደሆኑም አስረድተዋል።
በይቅርታ የተለቀቁ ታራሚዎች የበደሉትን ህብረተሰብና መንግስት እንዲክሱ፤ ህብረተሰቡም ታራሚዎችን ተቀብሎ ድጋፍ እንዲያደርግ ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡