ዓለምአቀፋዊ ዜና

አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

By Alemayehu Geremew

September 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ከሆኑት ማይክ ሀመር ጋር በጽኅፈት ቤታቸው መምከራቸው ተገለጸ።

በውይይታቸውም የኢትዮጵያና የአሜሪካ የሁለትዮሽ ጉዳዮች እንዲሁም ቀጣናዊ፣ አኅጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡