አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አብሮነት በሁሉም የስራ መስክ የድል መሰረት ነው ሲሉ በ19ኛው የቡዳፔስት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳታፊ አትሌቶች ተናገሩ።
ዛሬ የአብሮነት ቀን “በሕብር የተሰራች ሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ በመላ ሀገሪቱ ተከብሯል፡፡
የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት እና በ19ኛው ቡዳፔስት ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ለሜቻ ግርማ÷ ለሀገር መስዋዕትነት መክፈል ኩራት እንደሆነ ገልጿል፡፡
በቡዳፔስት የዓለም ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ውድድር በቡድን ስራ ትልቅ ሚና የነበራት አትሌት ፀሐይ ገመቹ በበኩሏ÷ ለሀገርና ህዝብ በማሰብ እስከመስዋዕትነት እንደምትሮጥ ነው የገለጸችው፡፡
በሻምፒዮናው በወንዶች ማራቶን የነሐስ ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ልዑል ገብረስላሴ÷ የሀገር ድል በመናፈቅ በማንኛውም ውድድር ላይ ዋጋ መክፈል እንደሚያስፈልግ ተናግሯል፡፡
በሴቶች ማራቶን ውድድር በ19ኛው የቡዳፔስት የዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ያስገኘችው አትሌት ጎይቲቶም ገብረሥላሴም ይህን ሃሳብ ትጋራለች።
በውድድሩ ኢትዮጵያውያን በአብሮነት በመስራት ከወርቅ እስከ ነሐስ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ብርቱ ትንቅንቅ ማድረጋቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
በቡዳፔስቱ ውድድር በአየር ጸባዩ ሁኔታ የተጠበቀው ውጤት ባይመጣም በአብሮነት እሴት አኩሪ ገድልና ድል ለማስመዝገብ በቡድን እንደሰሩ ተናግረዋል።
በቀጣይም የአብሮነት ስራቸውን በማጠናከር ለሀገር አኩሪ ድል ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!