የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

By Alemayehu Geremew

September 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለ2016 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ የ2016 አዲስ ዓመት የሠላምና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

በአዲሱ ዓመት በፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም በመንግስትና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አብሮ የመሥራት ባሕል የሚዳብርበትን ሁኔታ ለመፍጠር በትብብር እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ አስቻይ ሁኔታ የሚፈጠርበትን የፖለቲካ ምኅዳር ለማመቻቸት የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ነው የጠቀሰው፡፡

“አዲሱ ዓመት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ሠላምና መረጋጋት የሚፈጠርበት የሠላም፣ የደስታና ተድላ ዓመት ይሁን” ሲልም መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡