የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲሱ ዓመት ጥላቻን በማስወገድ ፍቅርና አብሮነት እንዲሰፍን መስራት ይገባል- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

By Melaku Gedif

September 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ2016 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም÷ ዓመቱ የሰላም፣ የፍቅር፣ የእርቅና የይቅርታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

አዲሱ ዓመት አዲስ እይታና አስተሳሰብ እንዲሁም የተሻለ እንድንሠራ ቃል ለመግባት ተጨማሪ እድል የሰጠ በመሆኑ በአግባቡ ልንጥቀምበት ይገባል ብለዋል።

ትውልዱ ሀገርን በአብሮነት ካጸኑ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ትምህርት በመውሰድ ለኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም መስራት እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ “ታላላቆች ልምዳቸውና እውቀታቸውን ለተተኪው ትውልድ ሊያስተላልፉ ይገባል” ብለዋል።

በመሆኑም አዲሱ ዓመት ጥላቻን በማስወገድ ፍቅርንና አብሮነት እንዲሰፍን የምንሰራበት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡