አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የረክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዕተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተከፈተ።
በጉባኤው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ይህ ወቅት ለሀገራችንም ለቤተ ክርስቲያናችንም ለህዝባችንም ከባድ የፈተና ወቅት ነው ብለዋል።