አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብፅ በሞሮኮ እና በሊቢያ በደረሱ አደጋዎች አጋርነቷን ለማሳየት የ3 ቀናት ብሔራዊ ሀዘን አወጀች፡፡
የግብፁ ፕሬዚዳንት አብድልፈታህ አል ሲሲ÷ የግብፅ ህዝብ በሞሮኮ እና በሊቢያ በደረሰው አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ልባዊ ሀዘኑን ይገልፃል ብለዋል፡፡
በወንድም ህዝቦች ላይ በደረሰው ጉዳትም በግብፅ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን ታውጇል ማለታቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል፡፡
ከሀዘን ቀኑ በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ የግብፅ ጦር በሞሮኮ እና ሊቢያ ለተጎዱ ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ርዳታ እንዲያቀርብ መመሪያ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡
ቀደም ሲል በሞሮኮ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀት 2900 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ በሊቢያ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ደግሞ ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች መምታቸው ይታወቃል፡፡