የሀገር ውስጥ ዜና

በመስከረም የመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት የአየር ሁኔታው ለግብርና ሥራ ምቹ ነው ተባለ

By ዮሐንስ ደርበው

September 13, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመስከረም ወር የመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት የሚኖረው የአየር ሁኔታ ለግብርና ሥራ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የአየር ሁኔታው ቀደም ብለው ለተዘሩ፣ ፍሬ በመያዝ ላይ ለሚገኙና ዘግይተው ለተዘሩ እንዲሁም በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሰብሎችም ሆነ ለቋሚ ተክሎች የተሟላ እድገት የሚያስፈልገውን የውሃ አቅርቦት ለማረጋገጥ አዎንታዊ ሚና ይኖረዋል ብሏል።

በአንጻሩ የእርጥበት ሁኔታው ከሰሜንና ከሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየቀነሰ እንደሚሄድና በሂደት እንደሚቆም ትንበያዎች ያመላክታሉ ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙና አልፎ አልፎ ከባድ ዝናብ ሊኖራቸው እንደሚችል ነው የተመለከተው፡፡

በዚሁ መሠረት አስቀድሞ ልዩ ትኩረትና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ኢንስትቲትዩቱ አሳስቧል።

በአንዳንድ ቦታዎችም በከባድ ዝናብ ምክንያት ውሃ ማሳ ላይ እንዳይተኛ፣ የውሃ መውረጃዎችን መሥራትና ነባር የሆኑ የፍሳሽ መውረጃዎችን ማጽዳት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!