አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሊቢያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች እና ጉዳት ለደረሰባቸው አካላት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጹ፡፡
በሊቢያ ምስራቃዊ ግዛት ደርና ከተማ ሰሞኑን በተከሰተ የጎርፍ አደጋ እስካሁን የ6 ሺህ ሰዎች ሕይወት ማለፉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁም ተመላክቷል፡፡