RemasterDirector_1a5c03258

የሀገር ውስጥ ዜና

በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የ3 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

By Shambel Mihret

September 14, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች የተመጣጠነ አመጋገብ ሥርዓትን ለማሻሻል የሚውል የ3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ድጋፉን የተፈራረሙት  የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የፈረንሳይ  መንግስትና ዓለም አቀፉ የሕጻናት አድን ድርጅት በኢትዮጵያ መሆናቸውን በኢትዮጵያ  የፈረንሳይ  ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ በግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ትግራይ ፣ አማራ፣ አፋር እና ኦሮሚያ ክልሎች የተመጣጠነ የአመጋገብ ሥርዓትን ለማሻሻል እንደሚውል ተመላክቷል፡፡